Fana: At a Speed of Life!

በተደረገው የፖሊሲ ማሻሻያ 3 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግስት ባደረገው የፖሊሲ ማሻሻያ ባለፉት ሰባት ወራት 3 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ መገኘቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስትሩ ከ200 በላይ ኩባንያዎች የሚሳተፉበትን 14ኛው የኢትዮ – ቻምበር ዓለም አቀፍ ንግድ ትርዒት በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል።

“የኢትዮጵያን ይግዙ” በሚል መሪ ሐሳብ ከመጋቢት 4 እስከ 8 ቀን 2017 ዓ.ም የሚካሄደውን የንግድ ትርዒት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ማዘጋጀቱም ተገልጿል።

የንግድ ትርኢቱ የንግዱን ማህበረሰብ ከሸማቹ ጋር በማገናኘት የምርቶችን ዋጋ ለማረጋጋት እንደሚረዳም ተመላክቷል።

መንግስት በሚያደርጋቸው የፖሊሲ ማሻሻያዎች ምክንያት የውጭ ምንዛሬ ገቢ መጨመሩን የገለጹት ካሳሁን (ዶ/ር)÷ ባለፉት ሰባት ወራት ብቻ 3 ነጥብ 84 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ በበኩላቸው÷ የንግድ ትርዒቱ የገበያ ትስስር ለመፍጠር ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለውም አመልክተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በሚካሄደው ዐውደ ርዕይ በዓለም ዓቀፍ የንግድ ተቋማት እና በሀገር ውስጥ ኢንተርፕራይዞች ምርቶች እና አገልግሎቶች መቅረባቸውም ተመላክቷል፡፡

በነፃነት ፀጋይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.