Fana: At a Speed of Life!

የፋይናንስ ተቋማት የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፋይናንስ ተቋማት የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ እደሚገባ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ገለጸ።

“የፋይናንስ ተቋሞቻችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የአየር ንብረት ፋይናንስ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል” በሚል መሪ ሐሳብ ከሁሉም የፋይናንስ ተቋማት አመራሮች ጋር በዛሬው ዕለት ምክክር ተካሂዷል።

በመድረኩ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ የአየር ንበረት ለውጥን ለመከላከል በምታደርገው ጥረት የአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል።

መንግስት የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም የሚያስችሉ ተጨባጭ ተግባር እያከናወነ ይገኛል ያሉት ሚኒስትሯ፤ ላለፉት ስድስት ዓመታት በውጤት የተጓዘውን የአረንጓዴ አሻራ አንስተዋል።

የሌማት ትሩፋትና የበጋ ስንዴ ምርት ወጤታማ ሥራ የተከናወነባቸው ዘርፎች መሆናቸውንም ለአብነት መጥቀሳቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.