Fana: At a Speed of Life!

በናንጂንግ በሚካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና 14 ኢትዮጵያዊያን ይሳተፋሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቻይና ናንጂንግ በሚካሄደው የዘንድሮው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክሉ 14 አትሌቶች እንደሚሳተፉ ተገለጸ፡፡

የሁለት ጊዜ የሻምፒዮናው ባለክብር መለሰ ንብረት እና ሳሙኤል ተፈራ በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር ኢትዮጵያ ይወክላሉ፡፡

በሪሁ አረጋዊ፣ ቢኒያም መሃሪ እና ጌትነት ዋለ በወንዶች 3 ሺህ ሜትር በናንጂንጉ የቤት ውስጥ ውድድር ላይ የሚሳተፉ አትሌቶች ናቸው፡፡

በሴቶች 800 ሜትር የአምናው የመድረኩ አሸናፊ ጽጌ ድጉማን ጨምሮ ሀብታም አለሙና ንግስት ጌታቸው እንደሚሳተፉ ታውቋል፡፡

ጉዳፍ ጸጋይ፣ ወርቅነሽ መሰለ እና ድርቤ ወልተጂ በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ናቸው፡፡

በሴቶች 3 ሺህ ሜትር ጽጌ ገብረሰላማ፣ ፍሬወይኒ ኃይሉ እና ብርቄ ሀየሎም እንደሚሳተፉ የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የ2025 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ከመጪው አርብ ጀምሮ ለሶስት ቀናት በቻይና ናንጂንግ ይካሄዳል፡፡

በኃይለማርያም ተገኝ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.