Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የሀገራዊ ምክክር አጀንዳ ማሰባሰብ በቅርቡ እንደሚጀመር ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል የተሳታፊዎች ልየታ በመጠናቀቁ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደትን በቅርቡ እንደሚጀምር አስታወቀ።

በክልሉ ባጠረ ጊዜ ውስጥ ወደ አጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ለመግባት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ መሆኑን የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ ጥበቡ ታደሰ ገልጸዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት በሕዝባዊ መድረኮችና በተለያዩ አማራጮች በአብዛኛው ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በስኬት መጠናቀቁን ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ በፌዴራል ደረጃ እንዲሁም በዲያስፖራ ማህበረሰብ የአጀንዳ የማሰባሰብ ሥራን ለማከናወን ዝግጅት እያደረገ መሆኑንም ቃል አቀባዩ ገልጸዋል፡፡

በፌዴራል ደረጃ ከሚገኙ ተቋማትና ማህበራት ተወካዮች የአጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረክ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ እንደሚካሄድም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በተጨማሪም ኮሚሽኑ በምክክሩ ሂደት እስካሁን የተሰባሰቡና በቀጣይ የሚሰባሰቡ አጀንዳዎችን የማደራጀትና የመቅረጽ ሥራዎች እንደሚያከናውን ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.