Fana: At a Speed of Life!

339 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 339 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ከየካቲት 27 እስከ መጋቢት 4/2017 ዓ.ም ድረስ በተደረገ ክትትል 281 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር የገቢ እና 57 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር የወጭ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች መያዛቸውን ነው ኮሚሽኑ የገለጸው፡፡

ማዕድናት፣ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ የቁም እንስሳት እና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ከኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል ይገኙበታል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌዴራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና በሕብረተሰቡ የጋራ ጥረት የተያዙ መሆናቸውንም የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 12 ተጠርጣሪ ግለሰቦች እና አምስት ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.