ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በየዓመቱ የሚያከናውኑትን የኢፍጣር መርሐ-ግብር አካሄዱ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ላይ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የኢፍጣር መርሐ-ግብር አከናውነዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየዓመቱ የሚያከናውኑት የኢፍጣር መርሐ-ግብር በቅርቡ በታደሰው ብሔራዊ ቤተመንግሥት መከናወኑም ነው የተገለጸው።
የኢፍጣር ተሳታፊዎች ብሔራዊ ቤተመንግስቱን መጎብኘታቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል።