Fana: At a Speed of Life!

አዋሽ ባንክ ለእስልምና እምነት ተከታይ ደንበኞቹ የኢፍጣር መርሐ-ግብር አካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አዋሽ ባንክ 1 ሺህ 446ኛውን የረመዷን ፆም ምክንያት በማድረግ በሸራተን አዲስ የጋራ የኢፍጣር መርሐ-ግብር አካሂዷል፡፡

ባንኩ መርሐ-ግብሩን ያካሄደው ለእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም ምኞቱን ለመግለጽና ለደንበኞቹ ያለውን አጋርነት ለማረጋገጥ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በመርሐ-ግብሩ ላይ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ፤ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፀሐይ ሽፈራውን ጨምሮ የአዋሽ ባንክ የሸሪዓ አማካሪዎች፣ የባንኩ የሥራ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

አዋሽ ባንክ ከዚህ ቀደም በክልል ከተሞች የኢፍጣር ፕሮግራም ያከናወነ ሲሆን፥ በቀጣይም በሰመራ እና በጅግጅጋ ከተሞች መሰል ፕሮግራም እንደሚያካሄድ ተገልጿል።

በተጨማሪም ባንኩ ለአወሊያ ትምህርት ቤት 5 ሚሊየን ብር፣ ለአንዋር መስጊድ የውሃ ቁፋሮ ሥራ የሚውል 7 ሚሊየን ብር እንዲሁም በተለያዩ ሆስፒታሎች ለሚገኙ የኩላሊት ህመምተኞች ህክምና የሚውል 11 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።

በሰአዳ ጌታቸው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.