ኮርፖሬሽኑ በግማሽ በጀት ዓመት 914 ሚሊየን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ስር የሚተዳደረው የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የ2017 ግማሽ በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በበጀት ዓመቱ 42 የግንባታ፣ 86 የፕሮጀክት ዲዛይንና 250 የሱፐርቪዥን ሥራዎችን በማከናወን 91 በመቶ የሥራ አፈጻጸም ማስመዝገቡ ተገልጿል፡፡
በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ 3 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ገቢ እንዲሁም 914 ሚሊየን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በረዥም ጊዜ ኢንቨስትመንቶች ላይ ትኩረት እንዲያደርግ እንዲሁም የፋይናንስ የውጭ ገበያ አማራጮቹን ማስፋት እንዳለበት በግምገማው ላይ ተጠቁሟል፡፡