በቀርሳ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን ቀርሳ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ።
አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ከዋታር ከተማ ወደ ቀርሳ ከተማ ሲጓዝ ከሞተር ሳይክል ጋር በመጋጨቱ የአራት ሰዎች ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።
የአደጋው መንስኤ ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር መሆኑን የመምሪያው የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኃላፊ ካስዬ አበበ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።
በነጌሶ ከድር