Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የፋይናንስ፣ የኢኮኖሚ ልማትና የፕላን ሚኒስትሮች ጉባዔ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን 57ኛው አህጉራዊ የፋይናንስ፣ የኢኮኖሚ ልማትና የፕላን ሚኒስትሮች ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

በጉባዔው ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ክላቨር ጋቴቴ፣ የአፍሪካ አሕጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ዋና ጸሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ፣ ሚኒስትሮች፣ የአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ጉባዔው“የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራን የሚያፋጥኑ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎችን መቀየስ”በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራ የአፈጻጸም ሒደትና የቀጣይ ተግባራት ላይ በመምከር አቅጣጫ ማስቀመጥ የጉባዔው ዋነኛ አጀንዳ ነው ተብሏል፡፡

ጉባዔው በባለሙያዎች ደረጃ ከመጋቢት 3 እስከ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ለሦስት ቀናት መካሄዱ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.