Fana: At a Speed of Life!

በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 53 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግሥት በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 53 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

ኢትዮጵያኑ ከማይናማር እገታ ወጥተው ታይላንድ ወታደራዊ ካምፕ የነበሩ ሲሆን ከኢትዮዽያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር ወደሀገራቸው ተመልሰዋል።

በዚህም በአካባቢው ከሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመነጋገር ትናንት 23 ዜጎችን እንዲሁም ዛሬ 30 ዜጎች በአጠቃላይ በካምፑ የነበሩትን 53 ዜጎች እንዲመለሱ ተደርጓል።

እስካሁን ከማይናማር እገታ ወጥተው ታይላንድ ወታደራዊ ካምፕ የነበሩ በመጀመሪያውና ሁለተኛው ዙር በጠቅላላው 130 ዜጎችን መመለስ መቻሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.