Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል ለምርት ዘመኑ 300 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ይቀርባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲዳማ ክልል ለ2017/18 የምርት ዘመን ጥቅም ላይ የሚውል የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ እየቀረበ መሆኑን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ምክትልና የግብርና ግብአት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ለገሰ ሀንካርሶ እንዳሉት፤ ለምርት ዘመኑ የሚሆን 300 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ እየቀረበ ነው።

እስካሁንም 70 ሺህ ኩንታል ዩሪያና ዳፕ የአፈር ማዳበሪያ የበልግ እርሻ ቀድሞ በሚጀመርባቸው አካባቢዎች ለሚገኙ አርሶ አደሮች እየቀረበ መሆኑን ገልጸዋል።

በሲዳማ ኤልቶ ዩኒየን በኩል በ121 ማሰራጫ ጣቢያዎች የአፈር ማዳበሪያውን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ መደረጉን መናገራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.