Fana: At a Speed of Life!

የታንዛኒያ የመከላከያ ኃላፊዎች የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደርን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የታንዛንያ ከፍተኛ የመከላከያ ኃላፊዎች የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደርን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም፤ የተቋሙን የታለንት ልማት ማዕከል፣ በራስ ዐቅም የለሙ የመረጃና ኮሙኒኬሽን እንዲሁም ሌሎች አስቻይ የቴክኖሎጂ ምርትና አገልግሎቶችን መመልከታቸውን የአሥተዳደሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

የአሥተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ ተቋሙ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት በራሱ ዐቅም እያለማቸው ስላሉ ምርትና አገልግሎቶች ለጎብኝዎቹ ገለጻ አድርገዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.