የሱዳን የሰላም ሂደት የልዩ ልዑኮች ፎረም ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሱዳን የሰላም ሂደት ልዩ ልዑኮች ፎረም ስብሰባውን ዛሬ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል፡፡
የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ልዩ ተወካዮቹ ለሱዳን የሰላም ሂደት ያላቸውን ቅንጅት እና ትብብር ማጠናከር እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡
ፎረሙ በሱዳን ሰላም ለማምጣት የሚደረጉ ጥረቶች የተቀናጁ እና የተናበቡ እንዲሆኑ የሚሰራ ሲሆን በሱዳን ያለውን ግጭት ለመፍታት የጋራ እና ግልጽ የአካሄድ ስልትን ለመፍጠር ያለመ ስለመሆኑም ኢዜአ በዘገባው አመልክቷል።
ኢጋድ የሰላም ሂደቱ በሱዳናውያን ባለቤትነት እና መሪነት እንዲከናወን በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጧል።