Fana: At a Speed of Life!

እየጣለ ያለው ዝናብ ለበልግ አብቃይ አካባቢዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሁኑ ወቅት እየጣለ ያለው ዝናብ ለበልግ አብቃይ አካባቢዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ፈጠነ ተሾመ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በነበራቸው ቆይታ÷ኢትዮጵያ ከክረምት ቀጥሎ ከፍተኛ ዝናብ የምታገኘው በበልግ ወቅት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሀገሪቱ ደቡባዊ አጋማሽ፣ ሰሜን እና ምዕራብ አካባቢዎች የበልግ ወቅት ዝናብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ነው ያስረዱት፡፡

የአሁኑ ዝናብ ለበልግ አብቃይ አካባቢዎች ከፍተኛ ጥቅም እንደሚሰጥ ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ÷ በተለይም በእንሰሳት እርባታ ለሚተዳደሩ አካባቢዎች ለመኖ አቅርቦት መልካም አጋጣሚ ይፈጥራል ብለዋል።

ቅጽበታዊ ጎርፍ በሚያጋጥማቸው አካባቢዎች ኢንስቲትዩቱ ለአርሶ አደሩ መረጃ በመስጠት ሰፊ ሥራ ሲያከናውን መቆየቱን አንስተዋል።

በከተማም የጎርፍ ማፋሰሻ ቦዮችን የማጽዳት እና ሌሎች ለጎርፍ ተጋላጭ የሚያደርጉ ሁኔታዎችን የመከላከል ሥራ መሰራቱን ነው የገለጹት፡፡

በመቅደስ ከበደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.