Fana: At a Speed of Life!

ሙያተኛንና ከፊል ሙያተኛን ወደ ሳዑዲ ለመላክ የሚያስችለው ስምምነት እንዲፈረም ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሙያተኛንና ከፊል ሙያተኛ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመላክ የሚያስችለው ስምምነት እንዲፈረም በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) ጠየቁ።

አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) ከሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ሳቀር አል ቆራሺ ጋር በሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም፤ የሀገራቱን የልማትና ኢንቨስትመንት ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በሳዑዲ ማቆያ ማዕከላት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር የማስመለሱ ሂደት በሁለቱም ወገኖች ትብብር ተጠናክሮ መቀጠሉ በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡

አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ ሙያተኛንና ከፊል ሙያተኛ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሳዑዲ ለመላክ የሚያስችለው ስምምነት እንዲፈረም ጠይቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.