Fana: At a Speed of Life!

ጅቡቲ ለኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት የመስሪያ ቦታ አበረከተች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጅቡቲ መንግስት በሀገሪቱ ለሚገነባው የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት መስሪያ የሚሆን አራት ሄክታር መሬት በስጦታ አበርክቷል።

በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፥ የመሬት ስጦታው የኢትዮጵያ እና ጅቡቲ መልካም ወዳጅነት ማሳያ መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

በመስሪያ ቦታው ላይ በቅድሚያ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ለመገንባት የገቢ ማሰባሰብ እና በስራ ሂደቱ ላይ ከኮንስትራክሽን ድርጅት ጋር ውይይት እየተደረገ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.