ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል:-
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል:-
👉 አሁን ላይ የፕሪቶሪያው ስምምነት ነጥቦች ተግባራዊነት ያለበት ደረጃ ምን ይመስላል፣ ማብራሪያ ቢሰጥ፣
👉 በትግራይ ክልል የሚስተዋለው ወቅታዊ ሁኔታ ወደ ግጭት እንዳያመራ እና ድጋሚ ዋጋ እንዳያስከፍል ምን እየተሰራ ነው፣
👉 ልዩነትን በውይይት የመፍታት ልምዳችን ደካማ ነው፣ ይህም በተለያየ ጊዜ ዋጋ ሲያስከፍል ይስተዋል፣ ስለሆነም መንግስት እና ገዢው ፓርቲ ልዩነትን በውይይት ለመፍታትና ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተሰራው ሥራ፣ የተገኘው ውጤት እና ቀጣይ አቅጣጫ ቢብራራ፣
👉 በተለያዩ ዘርፎች የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን በዘላቂት ለመፍታት በቀጣይ የሚቀመጡ አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያ ቢሰጥ፣
👉 የነዳጅ ዋጋ ድጎማ ቢደረግለትም በተለያዩ አካባቢዎች በእጅጉ እየጨመረ ነው፣ ለመሆኑ የነዳጅ ምርት በየጊዜው እየጨመረ መሄድ ምክንያቱ ምንድን ነው፣ የዘርፉን ሕገ ወጥ ንግድ ለመከላከልስ መንግስት ምን እየሰራ ነው፣
👉 የዋጋ ንረትን ለመቀነስ እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች ነው፣ በሌላ በኩል አሁን ላይ የመንግስት ሰራተኛ እና በዝቅተኛ ኑሮ የሚገኙ ዜጎች የኑሮ ውድነት ጫና አለባቸው፣ ይህን ችግር ለመቅረፍ በቀጣይ ምን ታስቧል፣
👉 አንዳንድ ነጋዴዎች ታክስ የመክፈል ላይ ውስንነት አለባቸው፣ የታክስ አከፋፈል ሥርዓቱም ድርድር ላይ የተመሰረተ እየሆነ መጥቷል፣ ይህን ለማስተካከል ምን እየተሰራ ነው፣
👉 ዘላቂ ሰላም ለማስፈንና ብሄራዊ መግባትን ለማምጣት የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር አንዱ ሲሆን በተለያዩ አካባቢዎች ደግሞ ሕግ የማስከበር ስራ እየተከናነወነ መሆኑ ይታወቃል፤ ሰላማዊ አማራጭ ቅድሚያ ከመስጠት አንጻር እና ሁለቱንም አቀናጅቶ ከመተግበር አንጻር መንግስት ምን እየሰራ ይገኛል፣ የተገኘው ተጨባጭ ውጤትስ ምንድን ነው፣
👉 ከስራ እድል ፈጠራ ጋር ተያይዞ ባለፉት ሳበት ወራት የተገኘው አፈጻጸም አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ያለው አንድምታ ምንድን ነው፣
👉 በሰላም እጦት ሳቢያ የተለያዩ አካባቢዎች በሕዝብ ላይ የሚደርሰውን አላስፈላጊ ስቃይና እንግልት ለመፍታት ምን እየተሠራ ነው?
በመላኩ ገድፍ