Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል:-

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል:-

  • ባለፉት ስምንት ወራት በዋና ዋና የኢኮኖሚ አመላካቾች ታላላቅ ስኬቶች ተመዝግበዋል፣
  • በቀጣይ የበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት ይህን ስኬት ማጠናከር ከተቻለ ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት ከ8 ነጥብ 4 በመቶ በላይ የኢኮኖሚ እድገት ታስመዘግባለች፣
  • ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ችግሮች ቢያጋጥሙም ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያ 8 ነጥብ 1 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግባች፣
  • በዘንድሮው ዓመት ብቻ በአነስተኛ አርሶ አደሮች የሰብል ሽፋን ከ17 ነጥብ 3 ወደ 20 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር ማደግ ችሏል፣
  • በኩታ ገጠም እንቅስቃሴ እስከባለፈው ዓመት 8 ነጥብ 7 ሚሊየን ሄክታር መሬት የተሸፈነ ሲሆን÷ ዘንድሮ ወደ 11 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር ማደግ ችሏል‹
  • በመኸር ወቅት እርሻ ብቻ 4 ነጥብ 2 ሄክታር መሬት በስንዴ ተሸፍኗል፣
  • በድምሩ በዚህ ዓመት ከ7 ነጥብ 7 ሚሊየን ሄክታር ያላነሰ በስንዴ ሰብል ተሸፍኗል፤ከዚህም ከ300 ሚሊየን ኩንታል ያላነሰ ምርት ይጠበቃል፣
  • በቡና እና ሻይ ምርትም የተሻለ ስኬት እየተመዘገበ ነው። ለአብነትም ባለፉት ስምት ወራት ብቻ ከቡና ወጪ ንግድ 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።”

በብርሃኑ አበራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.