Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በብሪክስ ከፍተኛ የኢነርጂ ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በብራዚል እየተካሄደ በሚገኘው የብሪክስ ከፍተኛ የኢነርጂ አመራሮች ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች እንደምትገኝ ተገለጸ፡፡

በስብሰባው በብራዚል የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ በብሪክስ መድረክ ውስጥ ያለውን ትብብር በማጠናከር፣ ለፕላኔታችን ቀጣይነት ያለው እና የበለፀገ የወደፊት ሁኔታን ለማረጋገጥ የኢነርጂ ደህንነትን አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

የ2030 የዘላቂ ልማት አጀንዳን ለማሳካት በተመጣጣኝ ዋጋ፣ አስተማማኝ በሆነ መንገድ፣ ዘላቂ እና ዘመናዊ ሃይል ማግኘት ወሳኝ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የረዥም ጊዜ ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት ስትራቴጂን ጨምሮ ሌሎች ሀገራዊ እቅዶችን እና ስትራቴጂዎችን መሰረት በማድረግ የፈፀማቸውን ውጤታማ ተግባራትም አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ ንፁህ እና ዘላቂነት ያለው ኢነርጂ ለማረጋገጥ እና ለማስቀጠል፣ የኢነርጂ መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት የሀገሪቱን የሃይል ፍላጎት ለማሟላት እና ክልላዊ ትብብርን እንዲሁም ውህደትን አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።

በብሪክስ መድረክ ውስጥ የኢነርጂ ትብብርን ለማጠናከር ምርጥ ተሞክሮዎችን፣ ልምዶችን እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ጅምሮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ለቡድኑ አባል አገራት ጥሪ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.