Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የኢትዮጵያን የድርጅቱ አባልነት ሒደት እንደሚደግፉ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት ተደራዳሪ ኮሚቴ ከዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኒኮዚ አዌላ (ዶ/ር) ጋር ተወያይቷል፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ የንግድ ድርድር ሒደት ዙሪያ ፍሬያማ ምክክር ማድረጋቸውን ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ኢትዮጵያ እስካሁን የሄደችበትን የሁለትዮሽ እና የባለ ብዙ ወገን ድርድሮች አፈፃፀም ለዋና ዳይሬክተሯ ማብራታቸውን ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ በሚቀጥሉት ጊዜያት በሚኖሩ የተናጠል እና የጋራ ርብርብ የሚያስፈልጉ ጉዳዮችን ማስረዳታቸውን ጠቁመዋል፡፡

ኒኮዚ አዌላ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ሆና ማየት ትልቁ ውጥናቸው መሆኑን ገልፀው፤ የትኛውንም አይነት ድጋፍ ለማድረግ እንደማይቆጠቡ አረጋግጠዋል፡፡

በሌላ በኩል ለአፍሪካ ቡድንና ለአባል ሀገራት የኢትዮጵያን የአባልነት ድርድር እንዲደግፉ ይፋዊ ጥሪ እንደሚያስተላልፉ ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.