Fana: At a Speed of Life!

ፊንላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድ ትሥሥር ማጠናከር እንደምትፈልግ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ሰመሪታ ሰዋሰው በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ሄሌና አይራክሲነን እና የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም፥ ፊንላንድ በተለይም በትምህርት ዘርፍ ለኢትዮጵያ ለምታደርገው ድጋፍ ሚኒስትር ዴዔታዋ አመሥግነዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለተሟላ የኢኮኖሚ ሪፎርም ቁርጠኛ መሆኗን አስታውቀው፤ ለማኅበራዊ ችግር ተጋላጭ የሆኑ ዜጎችን ተደራሽ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

አምባሳደር ሄሌና አይራክሲነን በበኩላቸው፥ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድ ትሥሥር ለማጠናከርና በዲጂታል ዘርፍ የኢንቨስትመንት ተሳትፎዋን ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላት አረጋግጠዋል፡፡

ፊንላንድ የኢትዮጵያን የልማት አጀንዳ ከግብ ለማድረስ በትብብር የምታከናውናቸውን የልማት ሥራዎች አጠናክራ እንደምትቀጥልም አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.