Fana: At a Speed of Life!

የቻይና ባለሀብቶች በተለያዩ አማራጮች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ከሆኑት ቼን ሀይ ጋር በሁለትዮሽ የሥራ ስምምነት ላይ በአርባምንጭ ከተማ ተወያይተዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ርዕሰ መሥተዳድሩ እንዳሉት፤ በክልሉ በርካታ የቻይና ድርጅቶች እና ባለሀብቶች በተለያዩ ልማታዊ ሥራዎች ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡

በተለይም በኮንስትራክሽንና በቡና ንግድ ትሥሥር እየተሠራ ያለው የጋራ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ማስገንዘባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

በቀጣይም በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች መሠማራት ለሚፈልጉ የቻይና ባለሀብቶች የክልሉ መንግሥት ሁኔታዎችን እንደሚያመቻች አረጋግጠዋል፡፡

አምባሳደሩ በበኩላቸው፤ በኮንስትራክሽን፣ ቴክኖሎጂ ልውውጥ፣ ቱሪዝም፣ የአካባቢውን የቡና ምርት ማስተዋወቅና የዐቅም ግንባታ መስኮች ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በስፋት መሥራት የምትፈልጋቸው ናቸው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ርዕሰ መሥተዳድሩ እና አምባሳደሩ በተገኙበት፤ የቻይናውያን የባህል ቀን በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተከብሯል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.