የአልጄሪያ የኢነርጂ፣ ማዕድንና ታዳሽ ኃይል ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የአልጄሪያ የኢነርጂ፣ ማዕድንና ታዳሽ ኃይል ሚኒስትር መሀመድ አርካብ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ሁለቱ አገራት በኢነርጂ፣ ማዕድን እና ታዳሽ ኃይል ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ሊያጠናክር የሚችል ውይይት ከተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።