በትምህርት ጥራት የታዩ ጉድለቶችን ለማስተካከል የመምህራን አቅም ማጎልበት ይገባል- እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በትምህርት ጥራት የታዩ ጉድለቶችን ለማስተካከል የመምህራን አቅም ማጎልበት እንደሚገባ የማዕካለዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለፁ፡፡
የክልሉ የትምህርት፣ የጤና፣ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት፣ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን እና የሴቶችና ህፃናት ቢሮዎች አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡
በመድረኩ የማዕከላዊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)÷ ከትምህርት ቢሮ አንፃር የትምህርት አመራሮችን እና የመምህራንን አቅም ለማጎልበት እየተሠራ ያለው ሪፎርም አበረታች መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በክልሉ ባሉ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች የሚሰጡ የማጠናከሪያ ትምህርቶችን ለመስጠት የተጀመሩ ጥረቶች በጥንካሬ የሚነሱ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በመምህራን፣ በርዕሰ መምህራንና በተማሪዎች አቅም ግንባታ ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚጠበቅም አቅጣጫ ተቀምጧል።
ከጤና ቢሮ አኳያ የማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህንን ማጠናከር፣ ድንገተኛ ወረርሽኞችን የመቋቋም ተቋማዊ አቅምን ማጠናከር፣ የአገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻል ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡
በተመሳሳይ፣ ከሴቶችና ሕፃናት፣ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ እና ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮዎች አንፃር ጥንካሬዎች እና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች መለየታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡