Fana: At a Speed of Life!

ዴንማርክ ለኢትዮጵያ ገበያ ተኮር እርሻ ልማት ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በገበያ ተኮር ኩታ ገጠም እርሻ ልማት ፕሮግራም ዙሪያ በኢትዮጵያ ከዴንማርክ አምባሳደር ሱን ክሮግስትራፕ ጋር ተወያይተዋል፡፡

የልማት ፕሮግራሙ የመጀመሪያ ዙር ትግበራ በዴንማርክ መንግስት ድጋፍ በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ስር የተከናወነ ሲሆን፥ በ2ኛው ምዕራፍ ትግበራ ዙሪያ መክረዋል፡፡

ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፥ ፕሮግራሙ በምዕራፍ አንድ ትግበራው ገበያ ተኮር ኩታ ገጠም እርሻን ለማስፋት ያበረከተውን አስተዋፅዖ በመጥቀስ ለዴንማርክ መንግስት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አምባሳደር ሱን ክሮግስትራፕ በበኩላቸው ፕሮግራሙ በሚተገበርባቸው ክልሎች ተጨባጭ ለውጦች መገኘታቸውን ገልጸው፥ በምዕራፍ ሁለት ትግበራ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

የመጀመሪያው ምዕራፍ በትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን በምዕራፍ ሁለቱ ትግበራ ቤንሻንጉል ጉሙዝና ሶማሌ ክልሎች እንደተካተቱ ተገልጿል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በቀጣይ በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.