Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ክልል ም/ቤት የዋና አፈ-ጉባዔ ሹመትንና ረቂቅ አዋጆችን አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው መደበኛ ጉባዔ የዋና አፈ-ጉባዔ ሹመትንና የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን አጽድቋል፡፡

ጉባዔው ወ/ሮ መሰረት ማቲዎስን የክልሉ ም/ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ አድርጎ የሾመ ሲሆን÷ተሿሚዋ የተጣለባቸውን ሕዝባዊ ሃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ቃለ-መሃላ ፈጽመዋል፡፡

በተጨማሪም አቶ ጁል ናንጋልን የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባዔ ሆነው መሾማቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በክልሉ የአመለካከትና የተግባር አንድነት ለማምጣት እንዲሁም ተጨባጭ ለውጥ ለማስመዝገብ የአመራር ሽግሽግ መደረጉ ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል ም/ቤቱ የኦዲት ግኝት የጋራ ም/ቤት ማቋቋሚያ ደንብ፣ የመንግስት ድርጅቶች ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ፣ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅና የተሻሻለው የጋምቤላ ክልል ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.