በሲዳማ እና ኦሮሚያ ክልሎች መካከል ያለው ወዳጅነት ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲዳማ እና ኦሮሚያ ክልሎች መካከል ያለው ወዳጅነት እና ትብብር ተጠናክሮ መቀጠሉ ተመላከተ፡፡
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳደር ሽመልስ አብዲሳ ሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ ገብተዋል፡፡
አቶ ሽመልስ ሐዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፤ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መሥተዳደር ደስታ ሌዳሞ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
በክልሉ በሚኖራቸው ቆይታ፤ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ድጋፍ በሲዳማ ክልል የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶችን እንደሚያስመርቁ ይጠበቃል፡፡