Fana: At a Speed of Life!

አርጀንቲና አራት ጨዋታ እየቀራት ወደ ዓለም ዋንጫ አለፈች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ አሜሪካ ሀገራት የ2026 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከብራዚል ጋር ጨዋታዋን ያደረገችው አርጀንቲና 4 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።

የአርጀንቲናን የማሸነፊያ ግቦች ዩሊያን አልቫሬዝ፣ ኢንዞ ፈርናንዴዝ፣ አሌክሲስ ማክ አሊስተር እና ጁሊያኖ ሲሞን ሲያስቆጥሩ፤ ብራዚልን ከሽንፈት ያልታደገች ብቸኛዋን ግብ ማቲያስ ኩንሀ ከመረብ አሳርፏል።

ይህን ተከትሎም የወቅቱ የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ አርጀንቲና 4 ጨዋታ እየቀራት ለ2026 የዓለም ዋንጫ ውድድር ማለፏን አረጋግጣለች።

አርጀንቲና ምድቡን በ31 ነጥብ ስትመራው፤ ብራዚል በ21 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

በሌሎች የደቡብ አሜሪካ ሀገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች፤ ኮሎምቢያ ከፓራጓይ 2 ለ 2 እንዲሁም ቺሊ እና ኢኳዶር ያለምንም ግብ አቻ ሲለያዩ፤ ቬንዙዌላ ፔሩን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡

በወንድማገኝ ፀጋዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.