Fana: At a Speed of Life!

 የንግድ ማህበራት በፖሊሲዎች ዝግጅት ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የንግድ ማህበራት በየጊዜው በሚወጠኑ የንግድ ፖሊሲዎች ላይ በነቃ ተሳትፎ ግብዓት እንዲሰጡ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ፡፡

እንደ አዲስ ከተዋቀረው የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የስራ አመራር ቦርድ አባላት ጋር ትውውቅ ያደረጉት ሚኒስትሩ፤ በወደፊት የስራ ትብብር ዙሪያ መምከራቸውን በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል፡፡

ማህበራቱ የግሉን ሴክተር የዲሲፕሊን፣ የሙያና የመፈጸም ብቃት ለማጎልበት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የንግድ ስርዓቱ ዘመናዊ፣ አካታችና ዓለም አቀፍ ዕድሎችን ለመጠቀም እንዲያስችል ማህበራቱ የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

የማህበሩ አመራሮች የወጪ ንግድ ማሳያ ማዕከልን መጎብኘታቸውንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.