Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ የአፍሪካ አህጉራዊ ትስስር እንዲጠናከር ድጋፍ እንደምታደርግ ገለፀች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሩሲያ የአፍሪካ ሀገራት የእርስ በርስ ትስስራቸውን ለማጠናከር የሚያስችል ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች፡፡

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረኪሂን ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በነበራቸው ውይይት ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ስለሚቻልባቸው መንገዶች እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት አፍሪካን በተመለከተ ሩሲያ ስለሚኖራት ሚና ምክክር አድርገዋል፡፡

በዚህ ወቅት አምባሳደር ኢቭጌኒ በአፍሪካ ሀገራት መካከል ትብብር እና ውህደትን ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ሩሲያ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።

መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው÷ ሩሲያ የአፍሪካን ለመደገፍ ያሳየችውን ቁርጠኝነት ማድነቃቸውን በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.