አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ የደጋፊዎች ድምጽ አሸናፊ ሆነች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሰሞኑን በተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በ1 ሺህ 500 ሜትር ርቅት የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቷ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ የደጋፊዎች ድምጽ አሸናፊ ሆናለች፡፡
የዓለም አትሌቲክስ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ ባጋራው መረጃ፤ ከደጋፊዎች ባሰባሰበው ድምጽ መሠረት አትሌት ጉዳፍ ማሸነፏን አስታውቋል፡፡
በዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና አሸናፊ ከመሆኗ በተጨማሪ በደጋፊዎች በመወደድ እና ከፍተኛ ድምጽ በማግኘትት የሻፒዮናው ክስተት ለሆነችው አትሌት፤ የእንኳን ደስአለሽ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
አትሌቷ 1 ሺህ 500 ሜትሩን የቤት ውጥ ሻምፒዮና 3 ደቂቃ ከ54 ሰከንድ ከ86 ማይክሮ ሰከንድ በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸለሚ መሆኗን መረጃው አውስቷል፡፡