Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ታዬ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የባንግላዲሽ አምባሳደር አሰናበቱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የባንግላዲሽ አምባሳደር ሲክደር ቦዲሩዝማንን አሰናበቱ።

አምባሳደሩ በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ እጅግ ደስተኛ እንደነበሩ ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያ ታሪካዊና ቀደምት ሀገር መሆኗን ተናግረዋል፡፡

በቆይታየም ኢትዮጵያውያን እንግዳ ተቀባይ መሆናቸውንና ሀገሪቱም ለኑሮ ተስማሚና ምቹ መሆኗን ተመልክቻለሁ ብለዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ማዕከል ነች ያሉት አምባሳደሩ፤ የአፍሪካ ሕብረት መስራች መሆኗን ገልጸዋል።

ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለቤት መሆኗና የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷ የዚሁ ማሳያ ነው ብለዋል።

ባንግላዲሽ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር ያላቸውን ታሪካዊ ግንኙነት ለማጠናከር ቁርጠኛ አቋም እንዳላትም አረጋግጠዋል።

በቆይታቸውም የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት የሚያጠናክሩ ተግባራት ማከናወናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ለአብነትም በኢኮኖሚና በሕዝብ ለሕዝብ ትስስርና መሰል ተግባራት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በቀጣይም የባንግላዲሽና የኢትዮጵያ ግንኙነት ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.