የረመዳን ወር የ27ኛው ሌሊት የተርሃዊ ሶላት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በታላቁ አንዋር መስጅድ የረመዷን ወር የ27ኛው ሌሊት የተርሃዊ ሰላት ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡
ጾሙ በተጀመረ በ27ኛው ሌሊት የሚደረገውን ይህ የተርሃዊ ሰላት ሥነ-ሥርዓት፤ ሕዝበ ሙስሊሙ በጉጉት የሚጠብቀው ነው።
በዚህ ሌሊት “ለይለቱል ቀድር” ሕዝበ ሙስሊሙ ሌሊቱን የሚያሳልፈው ለረጅም ሠዓታት ሶላት በመስገድ፣ በጸሎት ዝክር በማድረግና እንዲሁም የአላህን ይቅርታ እና ምኅረትን አብዝቶ በመለማመን ነው፡፡
በመራኦል ከድር