የኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ስልጠና ወጣቶች በዲጂታል ስነ ምህዳር በንቃት እንዲሳተፉ የሚያስችል ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ስልጠና ወጣቶች በዲጂታል ስነ ምህዳር ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉ የሚያስችል ክህሎትና እውቀት የሚያስገኝ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ (ዶ/ር) የኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ስልጠና ወጣቶች በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እና አምራች እንዲሆኑ የሚያስችላቸውን ክህሎት የሚያገኙበት መንገድ እንደሆነ ተናግረዋል።
ሥልጠናው ለወጣቶች አዳዲስ እድሎች እንዲፈጠርላቸውና ሀገሪቱ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ወደ ፊት እንድትራመድ እያደረገ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።
ወጣቶች የኮዲንግ ክህሎት ሲኖራቸው ሰፊ ወደ ሆነው የዲጂታል ዓለም በመቀላቀል በቀጣይ አገርን የሚጠቅም በርካታ መተግበሪያዎችን በራሳቸው ማልማት እንዲችሉ መንገዱን የሚያመቻች ዕድል እንደሆነም ገልጸዋል።
የአምስት ሚሊየን ኮደርስ ስልጠናን ከ580 ሺህ በላይ ሰልጣኞች እየተከታተሉ እንደሚገኙና ከ180 ሺህ በላይ ዜጎች ስልጠናውን በማጠናቀቅ ዓለም አቀፍ የምስክር ወረቀት መውሰዳቸው ተገልጿል።
በበላይ ተስፋዬ