Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የማስተር ካርድ የክፍያ ሥርዓትን አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዓለም አቀፉ የክፍያ ተቋም ማስተር ካርድ ጋር በመተባበር የማስተር ካርድ ክፍያ ሥርዓትን አስጀምሯል።

ባንኩ ያስጀመረው የማስተር ካርድ ክፍያ ሥርዓት በኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓትን ለማሻሻል እንደሚያግዝ ተገልጿል።

ስምምነቱ ዓለም አቀፋዊ ግብይቶችን ለመፈፀም የሚያስችል እንደሆነም ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዚህ በፊት ከማስተር ካርድ ጋር በፋይናንስ ዘርፍ በትብብር ሲሰራ መቆየቱም በዚህ ወቅት ተገልጿል።

ማስተር ካርዱን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ እና የማስተር ካርድ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ማርክ ኢሊዮት በጋራ አስጀምረውታል።

በየሻምበል ምህረት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.