Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ ሹመቶችን ሰጠ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሹመቶችን መስጠቱን አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት፡- ወ/ሮ አይሻ መሀመድ የአዲስ አበባ ከተማ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ የሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም አቶ ሰይፈ ደምሴ የከነማ ፋርማሲ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆን ተሹመዋል፡፡

አቶ አዋሌ መሐመድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ነብዩ ፍቃዱ በቢሮው የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ እንዲሁም አቶ ዳኛቸው ፈለቀ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኦፕሬሽንና አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡

በተጨማሪም አቶ መለሰ አንሼቦ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን የግብርና ኤክስቴንሽን ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ሆነው መሾማቸውን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.