Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተከናውነዋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት መከናወናቸው ተገለጸ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በምዕራብ አርሲ ዞን ገደብ ሃሳሳ ወረዳ በመስኖ የለማ የስንዴ ሰብልን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት እንደተገለጸው፤ በኦሮሚያ ክልል ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት በስፋት ተከናውነዋል።

በተለይም በግብርና ዘርፍ ምርታማነትን ለማሳደግ በተቀረጹ ኢኒሼቲቮች የአርሶ አደሩን ገቢና ምርታማነትን ማሳደግ እንደተቻለ ተነግሯል።

በበጋ፣ በበልግ እና በክረምት ወቅቶች ስንዴ ማልማት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ስለመፈጠሩም ተገልጿል።

ስንዴ በስፋት ከሚመረትባቸው የክልል አካባቢዎች መካከል ምዕራብ አርሲ ዞን ተጠቃሽ መሆኑ ተመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.