የማዕከሉ ሰልጣኝ ሴቶች በገበያ ተፈላጊ የሆነ ክህሎት ባለቤት እንዲሆኑ ይሰራል ተባለ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ’ለነገዋ’ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ሰልጣኝ ሴቶች በገበያ ተፈላጊ የሆነ ክህሎት ባለቤት እንዲሆኑ እንደሚሰራ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።
ሚኒስትሯ ከማዕከሉ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት፤ በማዕከሉ የሚሰለጥኑ ሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማላቅ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
በመሆኑም የማዕከሉ ሰልጣኞች በሥራ ገበያው ላይ ተፈላጊ የሆነ ክህሎት ባለቤት እንዲሆኑ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።
በክህሎት ልማትና ሥራ ዕድል ፈጠራ መስክ ያለውን አማራጭ ከመጠቀም ባሻገር የማዕከሉን አቅም ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲያድግ የሚያስችል ድጋፍ የሚደረግ መሆኑን መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።
በማዕከሉ የሚሰለጥኑ ሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማላቅ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ያደርጋል ሲሉ የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገልጸዋል።