Fana: At a Speed of Life!

በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውሮፕላኖችን አገልግሎት ላይ ለማዋል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና አርቸር አቪዬሽን በተለያዩ ዘርፎች በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውሮፕላኖችን በአየር ትርንስፖርት አገልግሎት ላይ ለማዋል እና በአርቸር ኤር የበረራ ፕሮግራም መሰረት በሌሊት የሚደረጉ የጭነት በረራ አገልግሎቶችን ለመስጠት ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ዘመኑ የደረሰበትን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ከማስቻሉ ባለፈም ለአየር ንብረት መጠበቅ የራሱ አስተዋጽኦ ያበረክታል መባሉን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.