Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ኢራን በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ አብሮ ለመስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መከሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በኢትዮጵያ ከኢራን አምባሳደር አሊ አክባር ረዜል ጋር ተወያይተዋል፡፡

አቶ መላኩ አለበል በዚህ ወቅት÷ ኢራን ከኢትዮጵያ ካላት ጉልህ የሁለትዮሽ ግንኙነት በተጨማሪ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ኢንቨስትመንትን በመሳብና በቴክኖሌጂ ትብብር አብሮ ለመስራት መነጋገራቸውን ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የኢራን አምባሳደር አሊ አክባር ረዜል ከሚያዚያ 19 እስከ ሚያዚያ 23 ቀን 2017 በቴህራን በሚደረገው “ሦስተኛው የኢራን እና የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮንፈረንስ” ላይ እንዲሳተፉ ለሚኒስትሩ ግብዣ አቅርበዋል፡፡

በኮንፈረሱም የኢኮኖሚ እና የንግድ ሚኒስትሮች እንዲሁም የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች የሚሳተፉበት መሆኑን ገልጸዋል።

አምባሳደሩ የሁለትዮሽ ትብብራችንን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል አስፈፃሚ ፍኖተ ካርታ ለመመስረት የሃሳብ ልውውጥ የሚካሄድበት አንደሆነ መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.