Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለፍቼ ጫምባላላ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ – ፍቼ ጫምባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ኢትዮጵያ በብዝሃ ማንነት፣ ባህልና እሴቶች የደመቀች፣ በህብረ ብሔራዊነት የተጋመደች ታላቅ ሀገር ናት ብለዋል፡፡

ፍቼ ጫምባላላ በረጅም የትውልድ ሰንሰለት ውስጥ እዚህ የደረሰ ድንቅ በዓል መሆኑን አንስተው፥ የሲዳማ ብሔር ባህላዊ መታወቂያ ቅርስ ከመሆን አልፎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሀብት ጭምር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የተጣላ የሚታረቅበት፣ ሩቅ ያለው ከቤተሰብ ጋር ለመሆን የሚሰበሰብበትና በአዲስ ራዕይና በአዲስ ተስፋ ወደ ነገ መሸጋገሪያ የሆነና ለሲዳማ ህዝብ ልዩ ቦታ ያለው በዓል መሆኑንም ነው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.