ርዕሳነ መሥተዳድሮች ለፊቼ ጫምባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተለያዩ ክልሎች ርዕሳነ መሥተዳድሮች ለሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላለ በዓል የእንኳ አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ እንኳን ለሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል አደረሳችሁ ብለዋል፡፡
በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆንም ተመኝተዋል፡፡
በተመሳሳይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሠ መሥተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ፊቼ ጫምባላላ፤ የአብሮነት፣ የአንድነትና የሰላም ተምሳሌት መሆኑን ባስላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት ገልጸዋል፡፡
በዓሉ የሕዝቦችን የእርስ በርስ መስተጋብር የሚያጠናክር የሲዳማ ብሔር ድንቅ እሴት ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
የፊቼ ጫምባላላ በዓል በሐዋሳ ጉዱማሌ በድምቀት በመከበር ላይ ይገኛል፡፡