አሥተዳደሩ የዒድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋራ
አሥተዳደሩ የዒድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋራ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር 1 ሺህ 446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ 100 ሺህ ወገኖች ማዕድ አጋርቷል፡፡
የአሥተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ባለፋት ሰባት ዓመታት ሰው ተኮር ሥራዎች ላይ በትኩረት መሠራቱን ጠቅሰዋል፡፡
የዛሬው የማዕድ መጋራት መርሐ-ግብርም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ወገኖች በዓሉን በደስታ እንዲያከብሩ በማሰብ የተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በረመዳን ወር ውስጥ 68 ሺህ ለሚሆኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ዜጎችማዕድ ማጋራት መቻሉም ተገልጿል፡፡
የማዕድ መጋራቱ ሚድሮክ ኢንቨስትመንትን ጨምሮ ሌሎች ባለሃብቶችን በማስተባበር የተደረገ ድጋፍ መሆኑም አስረድተዋል፡፡
በመሳፍንት እያዩ