ለኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የላቀ ውጤታማነት ተቋማት በቅንጅት እንዲሠሩ ተጠየቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የላቀ ውጤታማነት ተቋማት የተቀናጀና የተናበበ አሠራርን መተግበር እንደሚጠበቅባቸው የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል አስታወቁ፡፡
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምስት ክላስተሮች የ2017 በጀት ዓመት የስምንት ወራት አፈፃፀም እየተገመገመ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለውጥ ማምጣት የቻሉ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን በግምገማው ላይ የገለጹት አቶ መላኩ፤ የአምስቱ ክላስተር ኮሚቴዎች ለንቅናቄው ውጤታማነት ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውን ተናግረዋል፡፡
የአምራች ዘርፉ ዕድገት የሁሉንም ተቋማት ርብርብ እንደሚጠይቅ እና ለንቅናቄው የበለጠ ውጤታማነትም የተቋማት ቅንጅታዊ አሠራር ወሳኝ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የኢንዱስትሪ ሽግግርን ለማፋጠን የተጀመሩ ሥራዎች ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑን እና ይህን ማጠናከር እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምስቱ የክላስተር ኮሚቴዎች የመሠረተ ልማት፣ የፋይናንስ፣ የአቅም ግንባታና ምርምር፣ የኢንቨስትመንትና የግሉ ዘርፍ ናቸው፡፡