የፊቼ ጫምባላላ በዓል በስኬት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ የፊቼ ጫምባላላ በዓል በስኬት መጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ቶማስ ገለጹ፡፡
በዓሉ በተለይም በሐዋሳ ሶሬሳ ጉዱማሌ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በሚገኝበት የሚከበር በመሆኑ አስቀድሞ ዝግጅት መደረጉን ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡
በዓሉ በድምቀት ተከብሮ እንዲጠናቀቅ የክልሉ ማሕበረሰብ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመሆን የተቀናጀ ጥረት ማድረጋቸውን ጠቅሰው፤ ለዚህም ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓትም ከተለያዩ አካባቢዎች በዓሉን ለመታደም የመጡ እንግዶች በሰላም ወደየመጡበት እየተመለሱ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡