ለተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ተግባር ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በዝቋላ፣ ደሃና እና ሌሎች ወረዳዎች ለተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ተግባር ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አካባቢ ዝናብ አጠር በመሆኑ የተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ ተግባርን ይሻል ብለዋል።
የተከዜን ተፋሰስ በመስኖ የማልማት ሥራም በየደረጃው የሚገኝ አመራር እና የአካባቢውን ማህበረሰብ ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑን አስገንዝበዋል።
እኒዚህን ተስፋ ሰጭ ጅምር ሥራዎች ማጠናከር፣ ማስፋት እና በቀጣይነት መፈፀም እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
የብሔረሰብ አስተዳደሩ ጅምር ተግባራት ለሌሎች ዝናብ አጠር የኢትዮጵያ አካባቢዎች ትምህርት ሰጭ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡