Fana: At a Speed of Life!

በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በሕዝቦች መካከል መጠራጠርን ለመፍጠር የሚጥሩትን መከላካል እንደሚገባ አስገነዘቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጋራ በሆነች ሀገር በሕዝቦች መካከል መጠራጠርን ለመፍጠር የሚሹ አካላትን መከላካል እንደሚገባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡

ሚኒስትሩ ሰሞኑን በኢቢኤስ ቴሌቪዥን በቀረበችው ብርቱካን ተመስገን ዙሪያ በሰጡት መግለጫ፤ መሰል አጠራጣሪ ሥራዎች በዋዛ እንደማይታለፉ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ሰላም እንዳትሆን የሚፈልጉ አካላት እንዳሉ ጠቁመው፤ በሕዝብ ስም አጀንዳዎች እየተሰጡ መሆኑን አመላክተዋል።

በተለይም በአማራ እና ኦሮሞ ሕዝቦች መካከል ውጥረት እንዲነግስ የሚሹ ኃይሎች መሰል ተግባራትን የሚፈጥሩ ሆነው እንደሚታዩ አብራርተዋል።

የአማራ ሕዝብ በማያባራ ችግር ውስጥ ሲሻገር የቆየ እና ለመሰል ድራማዎች ሰለባ እንዲሆን የተደረገ በመሆኑ ተገቢውን ግምገማ በማካሄድ አቋም መያዝ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ኅብረ-ብሔራዊ በሆነች ሀገር በሕዝቦች መካከል ሰላም እንዲኖር ሁሉም እንዲሠራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሰለሞን በየነ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.