ፊቼ ጫምባላላ የአንድነታችን ወርቃማና ብርቱ ሀብል ነው – ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ፊቼ ጫምባላላ የአንድነታችን ወርቃማና ብርቱ ሀብል ነው ሲሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ።
የፊቼ ጫምባላላ በዓል ትናንት እና ዛሬ በሀዋሳ ተከብሯል።
በዓሉን አስመልክቶ ፕሬዚዳንት ታዬ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በዓሉ የኢትዮጵያ ባህላዊ ትውፊት ድምቀት፣ የሀሳባችን ጥልቀትና ልዕልና ነው ብለዋል።
ፊቼ ጫምባላላ የህብረታችን ውቅር፣ የጋራ ታሪካችንና የአንድነታችን ወርቃማና ብርቱ ሀብል ነው ሲሉ ገልጸዋል።