Fana: At a Speed of Life!

በማይናማር በሬክተር ስኬል 7 ነጥብ 7 የተመዘገበ ርዕደ መሬት ተከሰተ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ማይናማር በሬክተር ስኬል 7 ነጥብ 7 የተመዘገበ የርዕደ መሬት አደጋ ተከሰተ።

የአደጋውን መከሰት ተከትሎ የተዋቀረው የአደጋ ጊዜ ቡድን እንደገለጸው፤ በመሬት መንቀጥቀጡ እስካሁን የሟቾች ቁጥር በግልጽ ባይታወቅም በ100 የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸውን ሊያጡ ይችላሉ።

ርዕደ መሬቱ በቻይና፣ ታይላንድ እና ህንድ መከሰቱን የዘገበው ቢቢሲ፤ በዚህም በታይላንድ መዲና ባንኮክ በግንባታ ላይ ያለ ህንጻ በመደርመሱ 81 ለጉዳት መጋለጣቸውን ገልጿል።

የታይላንድ መንግስት የኮንስትራክሽን ሰራተኞቹን ከፍርስራሹ ለማውጣት ርብርብ እያደረገ መሆኑን ጠቅሷል፡፡

በርዕደ መሬቱ የማይናማር ጎዳናዎች የተሰነጣጠቁ ሲሆን በርካታ ህንጻዎች እና ድልድዮች ፈራርሰዋል።

በአቤል ንዋይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.